

በግራንድ ራፒድስ ሚቺጋን ወደምትገኘው አማኑኤል ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን በደህና መጡ! እኛ እግዚአብሔርን በእውነትና በመንፈስ ለማምለክ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለዓለም ሁሉ ለማወጅና አማኞች በጌታ ጸጋና እውቀት እንዲያድጉ ለመርዳት የተሰባሰብን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ነን ።
ታሪካችን
ጉዟችን የጀመረው በ2001 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) በግራንድ ራፒድስ እና በአካባቢው እንኖር የነበርን ወንጌላውያን አማኞች በአንድነት በመሰባሰብ በሕብረት እግዚአብሔርን ማምለክ ስንጀምር ነበር ። ይህንን ሕብረት ለተሻለ ዓላማና አገልግሎት ለማሳደግ በመስማማት፣ በእግዚአብሔር እርዳታ በ2003 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) መተዳደሪያ ደንባችንን አርቅቀን በአማኑኤል ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መጠሪያ በአዲስ መልክ መንቀሳቀስ ጀመርን ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር በታማኝነት መርቶናል።
የአገልግሎታችን ዓላማዎች
ቤተክርስቲያናችን በሚከተሉት ዓላማዎችና መርሆዎች ላይ የተመሠረተች ናት፦
-
እውነተኛ አምልኮ፦ አምልኮተ እግዚአብሔርን በእውነትና በመንፈስ ማካሄድ ።
-
የመንፈስ አንድነት፦ በመካከላችን የፍቅር ሕብረትን ማራመድና አንድነታችንን መጠበቅ ።
-
ደቀመዝሙርነትና ወንጌል፦ ወንጌልን ላልሰሙት ማዳረስ፣ ደቀመዛሙርትን ማፍራትና አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን መመሥረት ።
-
ማኅበራዊ አገልግሎት፦ ለእግዚአብሔር ክብርና ለሰዎች ጥቅም ምግባረ ሠናይ ሥራዎችን መፈጸም፣ በኅብረተሰቡ ውስጥ ጽድቅንና ፍትሕን ማስረጽ ።
አብረውን ያምልኩ
የእሁድ አገልግሎት ፕሮግራም:
የከሰዓት በኋላ አገልግሎት: 4pm - 6:30pm
ያግኙን
3334 Breton Rd SE
Grand Rapids, MI
ስልክ
(616) 840 1484
